Telegram Group Search
ካንቺጋ ጨዋታ ላይሆነኝ ልብሽ እድሜ ክፈል አለኝ
ላንቺ መች ሠስቼው ዘመኔን
ካንቺ መች አጉድዬው ሠውነቴን
ልብሽ እድሜ የጠየቀኝ

ሠብልዬን
ሞከርኩኝ በእህታ ላወጣው አልቀንስም አለኝ
በቃ ባለሱቅ ፍራንክ የለኝም ነገ እሰጥሃለሁ ሲጋራ አቀብለኝ
አንድ ሲጋራዬን ንፋሱ በላብኝ ትንታ እያነቀኝ
የጀማሪ ነገር የሳብኩት ጭስ መልሶ እኔኑ እያሳለኝ
እህ እህ እህህህህህህህህህህህህህህ

ትንባሆ ጤናን ይጎዳል😁


ሠብልዬን ....
እስኪ ነይ አንባ እንውጣና እንባ እናዋጣ
ፍቅር ለሌላት ከተማ ፍቅር ለተዋት ከተማ ነይ እንባ እናዋጣ
መኖር እየሻተ ለገደልነው ፍቅራችን ትንፋሽ ለነፈግነው
ለሡ ለሠቀቀናሙ ፍቅራችን ነይ እሡን በንባ እንድፈነው
ወይ እንባ ካነቃው ካጠራው ከጠራው
አልያ ካራቀው ከወሠደው እንዲያሸሸው
ነይ አንባ ወተን ለቅሷችንን እናውጣው
እሪ እንበል
ኡኡ እንበል
ስንተሻሽ ላቆሠልነው
ስንጫጫህ ላልሠማነው
ስንራመድ ገፍትረን ለጣልነው
ሲሰምጥ ለተውነው
ነይ እናንባ
ነይ የምልሽ ለረፍትሽ ነው በንባሽ እንድትፀጂ
በውስጥሽ ንፍር ውሃ ራስሽ አንዳትፈጂ
ነይ አንባ እንውጣና የሃዘን ሞሾሽን አውርጂ
ነይ እንባ አዋጪ


ሠብልዬን

@esubalew_sable
የኔ ዘመን ሠው በራሡ ደርሶ ካላመመው በቀር ማዘን ትቷል በርቼን ሸሽቷል
አሁን አሁን ከተማው ያስፈራኝ ይዟል ጎዳናዎቹ ላይ የሚታየው ሁሉ ያጎብጣል የምታየውን ለመሸሽ አይን የሚያየው አቶ ሲቅበዘበዝ ሰው ማጣት ክብሩን ነፍጎት ውስጥህን ያከስምብሃል
ጎዳናውን እሸሸው ይዛለሁ
ከተማውና ከተሜው
ከተማውና አከታተሙ ያስፈራል
ለኛ ካልሆነን ለማን ይሆን የሚከትመው

🍀🌼🥀
መሄድ የምችለው ይህን ያህል ነው አለኝ ቁና ቁና እየተነፈሰ አመዴ ብን አለ እንዴ ምን ማለትህ ነው ገና ይቀረናል እኮ
ምንም ያህል ይቅረን በቃ ከዚህ በኋላ እግሬን አላነሳም!
ግራ አጋባኝ ያሰብንበት ለመድረስ አስበን የተነሳንበት ጋ አልደረስንም ይቀረናል መለሰ
ይቅረና ለመድረስ ያሰብንበት ሁሉ ልክ ነው ማለት ነው እንዴ መንገዳችንን አረማመዳችንን አስተላለፍ አኗኗራችንን አይተን የምንሄድበትን መረዳት በመሄድ ውስጥ ያወቅነው በመንገዳችን የተረዳነው የመድረሻችንን ጥቁረት መድረሻችን እርካታን ሳይሆን መከራን እንደሚሰጠን መምጣታችን አመጣጣችን ካሳወቀን አስቤያለሁና መድረስ አለብኝ በሚል እልህ ይሉት ግትርነት መጋጋጥ መላላጥ አለብን ነው እምትለው ይልቅ ቆመን እናጢን እናስተውል ከአያያዛችን መድረሻችንን እናብሰልስለውና ወይ መንገዱን ወይ አካሄዱን ለውጠን ዳግም እርምጃችንን እናነሳለን በትግል የሚያልፍ ጊዜ ሳይሆን በማሰብ የሚያልፈው ጊዜያችን ነው ለመሆን የሚያበቃን ይልቅ መገንፈሉን ትተህ ሰከን ብለህ አስብ!
ብሎኝ በጥልቅ ሃሳብ ሰመጠ የነፍሴ አስተውሎት ልክ ይሆን ስጋነቴን ጠየኩ ዝም አለኝ ለማብሰልሰል ከነፍሴ ጎን አረፍ አልኩ......ማብሰልሰልም ሆነ

ሠብልዬን

@esubalew_sable
@esubalew_sable
ሠውን ፍፁም አውቀዋለሁ ለማለት ስንት አመት ይፈጅ ይሆን ወይስ በሰው እድሜ ልክ አይተመንም?
ያውም በፍቅር ያወቁት ከብዙ ውስጥ የመረጡትን ያለፈውን አደል አሁንንም አደል ነገንም ሲነጋ ያለውንም ሌላ መስከረም ሲጠባ ያለውንም ዘመን የሠጡትን አወኩት ታመንኩበት የሚባለው እንዴት ይሆን ፍቅር ያላበጀው ልብን ቀለበትና ቃል ከምንስ ይሆን የሚከልለው ?

ወደ መኖር ልመለስ ለኔ ወደፊት የሆነ ለሚያየኝ ወደኋላ ወደሚመስለው መኖሬ
ልክ ነው ብዬ ልክ የሆኑኩት ሁሉ ብክነትና ሞኝነቶ ሆኖ ራሴን ነደለኝ አላሸውም እምምም ያርገኝ ለመዳን ህመም ለመሙላት መጎደል ያስፈልጋልና

ማንም አልተሳሳተም ሁላችንም ልክ ነን አረ ግራ ነው ቢለኝ ልክ ነው እሡ ቆሞ ካየበት ግራ ነው በኔም በኩል ቢሆን ቀኝ ያለው ግራ ነውና

ችርስ ለነበሩን ችርስ ለምንሄድበት ችርስ
እነሆ ዝምታ ሆነ ቃል ፈጥሮን ቃል ገደለን ዝም ዝም ወዳጆቼ ቃል ለካ ያረጃል ያውም ጅጅት ብሎ እናወራው ጠፋን የምናወራው አስፈራን የምለው ብርሃን አጣ ለካ ተቀባዩ አንፀባርቆት ኖሯል ቀድሞውንም የበራ
ያመኝ የነበረ አያመኝም ተውኩት
ያስታማሚ ነገር ሲቸግር አየሁት
ዝም ማለት እምር ብሎኛል ሁሉን ነገር እርግፍ አርጎ መተው ከአዲስ መጀመር ወይ አለመጀመር ዝም ብሎ መኖር ደስታህ አይቆይ ብሎ ማን እንደረገመኝ አላውቅም እናቴ እንኳ ግንባሬን ስማ የልቧን ሁሉ መርቃኛለች ለኔ ላልኩት የምችለውን ሁሉ ሆኛለሁ ባልችልም መዋጥ ባልቆርጥ እንኳን መወሠን አለብኝ በቆራጣ እግር እንዴት እንደሚኖር እንደመልመድ ይሆን እንጇ!
ያ ባለቅኔ እንዳለው

አለ አንዳንድ ውበት
አለ አንዳንድ ሙቀት
አለ አንዳንድ ፍቅር
ሲኖር ትዝ የማይል
ሲያጡት የሚያጎድል እንደ እጅና እግር።
ስንለይ እንዲህ ነው ብትንትን
አብረን አንዳልሆንን አንዳልከረምን
የሚይዘን እንደሌለ የኖርነውም እንዳልነበረ
እንዲሁ ልይትይት ፍርስርስ ድርምስምስ
በቃ?!
ቀትር ሆኗል። ካንዲት ወዳጄ ጋ ለቡና ተገናኝተን የባጥ የቆጡን እየዘባረቅን ከአንድ ካፌ በረንዳ ላይ ተቀመጥን ድክም ብሎኛል መንገዱ ሳይሆን ወሬዋ ዛልልልልል ። ውዴ የኔ ፍቅር እያለች ነው እምታወራኝ ትውውቃችን ደሞ የቀናት እድሜ ነው ያለው ይህ ቃል ደሞ ምኗም ላልሆንኩ እኔ ለምን? አኔ ደሞ እንዲህ ከይነቱ መለፋደድ አቤት ሲያደክመኝ ። ምን ልታዘዝ ? ብና አልኳት ባዶውን
ባዶ ብና አይከብድም ? /መቼም ካንቺ በላይ አይከብድም በውስጤ/ ባዶ ነው የምጠጣዎ ላንቺ ተዘዚያት ! ማኪያቶ አርጊልኝ ነጣ ያለ ።
እና እኔ ምልህ ውዴ አንዴት ነህልኝ
እንዴት ነኝ ልበላት
ማውራት ቀጠለች መስሚያዬም ዛለ ከካፌው የሬድዮ ስፒከር ቀልቤን ሰደድኩት ቀልቤን የሚጠፍር ሙዚቃ ሠማሁ ላለመስማት ሞከርኩ አልቻልኩም ውስጤን እንዴት አልስማ?
ሙዚቃው ቀጥሏል.....

እየጠፋሽኝ ነው ወይ እየጠፋሁሽ
ሠው በሰማሽ ቁጥር ዛሬም የምገርምሽ
ግራ ነው ለወሬ ልብን ከከፈቱ
እንደምኞት ላይሆን የህልም አፈታቱ
ልቤ እያወቀው እንዳላጠፋሁ
ባንቺስ እይታ መቼ ተከፋሁ
/አብራኝ ያለችው ሴት መኖሯን ዘነጋሁ /
እንዳልቀየምሽ ነገር ፈራሁ
ለሠው እንዳልወቅስሽ ደሞ ኮራሁ
ካነሰ ላንቺ መውደዴ
ማይ አይኔን እያየሽ ውዴ
እንዲህ ሲቀያየር ደርሶ አመልሽ
አንደበት አለሽ ወይ ምነው ብልሽ
ታዘብኩት አቅሜን በፍቅር
ሲከብደኝ ቀላሉ ነገር
ተስፋ ባጣ ባመንኩት ቃል እየተገረምኩኝ
አታውቀኝም ብዬ ጠረጠርኩኝ
ሰው ያለ እምነት ስም የሌለው እንደ ውሃ ቀለም
በህልም አለም አለ ያሉት የለም
የለም የለም የናፈኩት ሠውነት
የለም የለም ያፍቅራችን ያ ሁሉ አለም ተይ በይው ግድ የለም .....
/ለካ እስካሁን እያወራች ነው አይደል አለችኝ አዎ አልኳት ምኑን እንደ ሆነ እንጇ ማውራቷን ቀጠለች አስተናጋጇ ብናዬን ከፊቴ አስቀምጣ ሄደች እሷም ወሬዋን ቀጠለች እኔም ጆሮዬን ለሙዚቃው ሰጠሁ/...

ግድ ባይል እንኳ ልብሽ ለምነት
ወሬ አይበልጥም ነበር ካለኝ እውነት
አዘንኩኝ ከቶ መንገሱ ከውሸት ሃቄ ማነሱ
መታመኔን እንጂ ባለኝ አቅም
የሚፀፅት ነገር ባንቺ አላውቅም
ባመንኩት ፍቅር ስቀጣ
ገረመኝ ሰው ዞሬ ሳጣ
ተለያዩ ሲሉ መስማት ውስጤን እያመመው
ይሁን ብዬ የለም የማልሆነው
ባፍ አንግባ ብዬ ብስቅ ደስታ ሁሉ አይደላም
በህልም አለም አለ ያሉት የለም
የለም የለም የናፈኩት የማውቀው ሰውነት
የለም የለም ያ ፍቅራችን ያ ሁሉ አለም በይ ተይው ግድ የለም...

የዘፈኑ እያንዳንዱ ግጥም ውስጤን ጠረቆሰኝ የኔን ውስጥ ጥያቄና መታመም ዘፈን ሆኖ ሠማሁት የእውነት ውስጤ ተነፈሠ ... እየሠማሀኝ አደለማ አለችኝ ድካም የሆነች ልጅ እ አረ ተደናበርኩ ቡናዬ ክፉኛ ቀዝቅዟል ሳያት ልጅቷ ቀፈፈችኝ ፈራኋት ከሷ ህመሜን መረጥኩት ተነሳሁ ሂሳብን ከጨረጴዛው ላይ አስቀምጬ ከካፌው መውጣት ጀመርኩ የልጅቷ የጥሪ ድምፅ ከኋላዬ ይሰማል ....ባለው....አንተ እሡ.... አልዞርኩም አልዞርምም ቀጥ ብዬ ከራስ ህመሜ ጋ መንገዴን ተያያዝኩት ሙዚቃው ጆሮዬ ላይ አለ

የለም የለም ....... የናፈኩት የማውቀው ሰውነት

ህህህህህህህህህ
ለምን ያይሻል ሰማይ አዘቅዝቆ
የደመና ድጉን ፈቶ እራሱን አርቅቆ በፀሃይ አጮልቆ
ሙቀት ሆኖ ሊዋሃድሽ ፀሃይ ሠም ሆና እምቀልጥልሽ
በደመና ምስል ገፅሽን እሚስልሽ አንቺን እሚኩልሽ
ሠማይ አደብ አቶ ሲከተልሽ
ፀሃይ አንሳ ስታልቅልሽ
ደመና ተበትኖ ሲስልሽ
ተፈጥሮ ቅጥ አንባሯ ታጣን ባንቺ ልክ ተሰፋች
ንፋስ አንቺን ይዛ አለፈች
አደይ ባንቺ መልክ ፈካች
ባህር በልክሽ ፈሰሰች
የሠአሊ ገፁ ያንቺን ምስል ቀባ
የደራሲ ብዕር አንቺነትሽን ተፋ
አንቺን ከኔ ሊወስድ አደል አለም የሚለፋ!?



ሠብልዬን
ለምን እንደዚህ ሆነ....?
የሷ ፍቃድ እንደዛ ስለሆነ !
የሷ ፍቃድ ምንድነው ?
የፈቀደችው ::
የፈቀደችውስ ምንድነው ?
የሆነው !
የሆነዎ ምንድነው ?
እየሆነ ያለው ::
😏😏😏
ጅላንፎ ሃሳብ አስባችሁ ታውቁ እንደሆን እንጃላችሁ ☺️

ሠሞኑን ግን እንዲያ ያሳስበኝ ይዟል ኸረ እንደው ወዲያልኝ !!
መሞከር አይከፋም ብለን የሞከርናትን ትቃመሱልን ዘንድ ይዘን መተናል መልካም ምልከታ ተመኘሁ ባጠፋን እንክሳለን !👇
Forwarded from ስለ እናት
ሠው በእለት ይገነባል ሠው ሲያፈቅር መኖር ይጀምራል በቃ ሠው ሲያፈቅር ከእለት አልፎ አመታትን ያልፍል ሠማያትን ይዘልቃል ፍቅር ዛፍ ነው ሰው ደሞ ለእረፍት ከዛፉ ስር የሚያርፍ የጥላው ተጠቃሚ ነው
ስለ እናት
https://youtu.be/R_vWjSlSKOQ
ሸፋፋ ብትሆንም ብትንሸዋረርም እንደ አቅም ነውና መጀመሪያችንን ታዘብልን ብለን እነሆ በረከት አልን👆
2024/06/29 13:08:40
Back to Top
HTML Embed Code: